tg-me.com/nibab_lehiwot/171
Last Update:
የእኔ ታሪክ (ምዕራፍ 2)
ክፍል -12
ሕዝቅኤልን አረጋግታ ካስቀመጠችው በኋላ ሜሮን ታሪኩን መናገር ጀመረች። አሌፍ ብሎ ስሙን ያስቀየረው አባቱ ነው።ምክኒያቱም ከሌሎቹ ልጆቹ አስበልጦ በሚባል ደረጃ በጣም ይወደው ነበር። ከልጆቹ አንዱ ኡስታዝ እንዲሆን ይመኝ ስለነበረ ሰሚር ደሞ እንደሚፈልገው አይነት ብሩህ አእምሮ ስላለው ገና በልጅነቱ ነው ቁራን መቅራት የጀመረው ፍጥነቱ ሼሆቹኝ ሳይቀር አስደንቋቸው ነበር። ያም ሆነ ይህ ግን አሌፍም ይሁን ሰሚር የአንተ ልጅ ነው። በህይወቴ እንደዚህ አይነት የነገሮች ግጥጥም አይቼ አላውቅም ።ሕዝቅኤል መንቀጥቀጥ ጀመረ።ሜ....ሜሮን አ ልገባሽም ቪ..ቪቪያን እና አሌፍኮ.... ተናግሮ ሳይጨርስ ራሱን ስቶ ወደቀ። ሜሮን ጮኸች....ቪቪያን........አንተ ሕዝቅኤል ....ቪ ቶሎ ድረሱ እያለች ማልቀስ ጀመረች። ቪቪያን እና እናቷ ጩኸቱን ወደሰሙበት ሮጡ ሕዝቅኤል ተዘርሮ ወድቋል። አባዬ......ቪቪያን ጮኸች....እናቷ ይባሱኑ ስታየው ደርቃ ቀረች ። ሜሮን ለአምቡላንስ ደውላ ሕዝቅኤልን ወደ ሆስፒታል ወሰዱት ።
የሜሮን ወንዱ ልጇም ያለችበትን ነግራው ወደ ሆስፒታል እየመጣ ነው። ድንገት የሆስፒታሉ በር ላይ ሰማያዊ አይኖች ያሏት ፀጉሯ በጀርባዋ የወረደ ልጅ እንባዋን እንደጎርፍ እያወረደች ተመለከታት። ሲያያት አንጀቱን በላችው.....አድርጎት የማያውቀውን አጠገቧ ተቀመጠ። ግን ምን ማድረግ እንዳለበት ስላላወቀ ዝም ብሎ ያያት ጀመር። ለትንሽ ደቂቃ ትኩር ብሎ ሲያያት ከቆየ በኋላ ለምንድን ነው ምታለቅሽው አላት ቃላቱን በመከራ እያወጣ። ልጅቷ ጭራሽ አጠገቧ ሰው እንደተቀመጠ አላስተዋለችም ነበርና ደነገጠች። እንባዋን እየጠራረገች አይ ምንም አለች(የጠረገችው እንባዋ ወዲያው እየሞላ) ። ይኸውልሽ ምን እንደሆንሽ አላውቅም ግን ያለምክንያት እንደማታለቅሽ አውቃለሁ ። ምንም ይሁን ምን ግን ጠንካራ መሆን አለብሽ ። የምታስታምሚው ሰው የአንቺ ጥንካሬ ያስፈልገዋል። ከመድሃኒት በላይ የሰውን ልጅ የሚያድነው ተስፋ እና ብሩህ ፊት ነው እሽ....ስለዚህ ሁለተኛ እንዳታለቅሽ .....ልጅቷ ፈገግ አለች አወ ልክ እንደሱ ብሏት እሱም ፈገግ እያለ ትቷት ወደውስጥ ገባ።
እማዬ አላት ወዳለችበት እየሮጠ። ሜሮን ተቀምጣ እያለቀሰች ነበር። ምንድን ነው እናቴ አጎቴ ምን ሆነ አላት እያቀፋት። ደህና ነው ልጄ ና ቁጭ በል እዚህ አለችው አጠገባ ያለ መቀመጫ እየጠቆመችው። ኤልሳ በጣም ደንግጣ ስለነበረ እንዲያረጋጋት ወደሷ ላከችው። እሱም የሜሮን ልጅ እንደሆነ ተዋውቋት አጠገቧ ከተቀመጠ በኋላ ከልብ በሆኑ ቃላቶቹ አረጋግቷት ተመለሰ። ሜሮን ሁሌም እሱን ስታይ የሚያስታውሳት አንድ ሰው አለ። ሙሉ በሙሉ በእሱ እምነት አላት። ኤልሳም ሜሪ ልጅሽን ፈጣሪ ይባርከው አለቻት ፈገግ እያለች። ቅድም ውጭ ያያት ልጅ ራሷን አረጋግታ ከውጭ ስትገባ ተመለከታት። ምክሬ ሰራ ማለት ነው አለ ከልቡ ደስ እያለው።
እማዬ አለች ቪቪያን አባቷ ወደተኛበት ክፍል እየተመለከተች። ነይ እዚህ አባትሽ ደህና ነው ይልቅ ሰው ላስተዋውቅሽ አለቻት ። ቪቪያን ዞር ስትል የምታውቀውን ልጅ አየችው። እሱም አያት ያውቃታል...... ተዋወቁ የ ሜሪ ልጅ ነው አለቻት። ቪቪያን ለሰላምታ እጇን ዘረጋችለት። ማቲያስ አላት እጇን እየጨበጠ ቪቪያን አለችው እሷም ፈገግ ብላ። (የማቲያስ እና የሜሮንን ታሪክ ከአባቷ በደምብ ስለምታውቅ በስሙ ገረማት)።
አንቺ አልቃሻ አላት ቀስ ብሎ ቪቪያን እንደማፈር ብላ ወደ ክፍሉ ዞረች።
አሌፍም የሕዝቅኤልን መታመም ሰምቶ ሊጠይው ወደ ሆስፒታል ሲገባ ቪቪያን እና ማቲያስ እያወሩ ተመለከታቸው።
ይቀጥላል............
@nibab_lehiwot
BY ሕይወትን - በገፅ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/nibab_lehiwot/171